Tuesday, August 22, 2017

የመጽሐፍ ምርቃት ግብዣ


ብዙ የግጥም ውድድሮች አሸናፊ የሆነው ዘነበ ታምራት ከረጅም የሕይወት ልምድ በመነሳት እነሆ ግጥሞቹን ለአንባቢያን በትህትና ያቀርባል። ግጥሞቹ ስር ሰደድ ማሕበራዊ ችግሮችን በማንሳት ትችቶችን፤ እርማቶችን በምክር፤ በግሰጻ፤ በማሳመን በማባበልም ጭምር ጥልቅ መፍትሄዎችን ጠቅልለው ለምግበ-አእምሮ ያቀርባሉ።

እያዝናኑና እያሳሳቁ ቁም ነገር ያስተምራሉ። የዘመናችንን የማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በነገረ-እርክሪቲክመልክ ለመጭው ትውልድ ትምህርት ይሆኑ ዘንድ ያስተላልፋሉ።

የመጽፏ ዓላማ ልምዱ እይተለወጠና እየከፋ በመሄድ ላይ ያለውን የሕብረተሰባችን አስከፊ ገጽታ  ሃይ ብሎ ለመመለስ፤ የአስተዳደር በደልን በምክርና በግሳጼ ለመቅረፍና በሕግ የበላይነት የሚተዳደር ሕብረተሰብ እንዲፈጠር መገፋፋት ነው።



የመጽሐፍ ምርቃት ግብዣ
________________________________________________________
የማክበር ሰላምታዬን እያቀረብኩ “የሰው ሰውነቱ” በሚል ርእስ ያቀረብኩትን “የቅኔ ማዕበል“ መጽሐፍ ሴፕቴምበር 3 ቀን 2017 ዓ/ም 3.00 PM በመሶብ ሬስቶራንት አዳራሽ ስለማስመርቅ በቦታው ተገኝተው የምርቃቱ ተካፋይ እንዲሆኑ በማክበር ጋብዤዎታለሁ።
ከልብ ከመነጨ ሠላምታ ጋር
ዘነበ ታምራት ገብረማርያም
የዝግጅቱ ቦታ አድራሻ
መሶብ የኢትዮጵያ ባሕል ምግብ ቤት
1041 S. Fairfax Ave.
Los Angeles, CA.90019
Tel. 323 938 8827
አቶ ዘነበ ታምራትን ለማግኘት ከፈለጉ
ቴሌፎን 310 774 6007
e-mail ztamira@ yahoo.com             
የመጸሐፉ ዋጋ $ 12.00 ብቻ



Ethiopian Flag Coloring Page - Viewing Gallery

Friday, August 18, 2017

የአብርሃም በጎች ነን

                                               ዘነበ ታምራት ገብረ ማርያም

ቀን ጠባ ቀን መሸ ለኛ ምን ፋይዳ አለው
መጎተት መታሰር የቀን ውሏችን ነው
መቀጥቀጥ መደብደብ ቁርስ ምሳችን ነው
ካለፍርድ መረሸን የበየኑብን ነው
አቤቱታ ሰሚ ኧረ የት ነው ያለው
የዓለም ማሕበሩ ኒውዮርክ ላይ ያለው
የተመድ የሚሉት ሺባ ድርጅት ነው
የዓለም ፍርድ ቤቱ ዤኔቫ ላይ ያለው
ወይንስ ዋሽንግተን ኸዋይት ሃውስ ነው
አቤት የሚባለው
ለዓለም ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ ነው
ወይንስ ለአምኔስቲ የመብት ተሟጋች ነው
አቤቱታ ሰሚ ተው በቃ የሚለው
ሕዝብን ከአምባ ገነን ቀጥቃጭ የሚያድነው
የትኛው ማሕበር የትኛው ተቋም ነው
አምባ ገነን ከቶ በማን ነው እሚዳኘው
በጴጥሮስ ጋሊ ነው
ወይ በአሜሪካኑ በቢል ክሊንተን ነው
እየተቀጠቀጥን በአምባገነን በትር
ሰለባ እየሆንን ለወያኔ አሩር
የፍርድ ያለህ እያልን የምንጮኽ ዘወትር
ጠፍቶን አኮ አይደለም አፀፋ መሰንዘር
ነገር ግን ታጋዮች እመዐሕድ ውስጥ ያለን
ፍጹም ንጹህ ዜጎች በሰላም የምናምን
ለመስዋእት የቀረብን የአብርሃም በጎች ነን
የምንገደለው በጨለማ በቀን
ደማችን የሚፈስ ለአገር ለወገን
ሺበሺ እያለቅነ ወደኋላ የማንል
አጥተነው አይደለም የጫካውን ትግል
ነገር ግን ነን እኛ መተኪያ የሌለን
የቁርጥ ቀን ልጆች ኸመዐሕድ ያለን
የአገር ፍቅር እሳት የሚያንገበግበን
ትውልደ አማራ ፤ የሰላም አርበኞች ፤ የአብርሃም በጎች ነን
ሆኖም ችለን፤ ችለን፤
እምብየው ካላችሁ መላ እንመታለን፤
ካችአምና ያኘክነውን ዘንድሮ እንውጣለን፤
በገድሎ መጣሉ እንበልጣለን እንጂ መች እኛ እናንሳለን።
በአብሮ መኖር አምነን ዛሬም እንደ ጥንቱ
ነው ብለን ነው እንጂ የሰላም ሰብሃቱ
አቤት የምንለው በየአደባባዩ፤ በየፍርድ ቤቱ
መች ጠፋን ከቶውን ለእኛ ወንድነቱ
ነገር ግን አያልቅም የአማራ ትግስቱ
እኛ በትእግስት መላ እናፈላልግ እናንት ጮቤ ምቱ
ተመድ ነው ዋይት ሃውዝ የሚቀርብ ሙግቱ
ክስ የሚቀርብበት የት ነው ፍርድ ቤቱ
ኸዋይት ሃውዝ ነው ዋና ጽሕፈት ቤቱ
ወይንስ ከስተጀርባው ኸመኖሪያ ቤቱ
ኸፕሬዘዳንቱ?
የትነው መሟገቻው እንዴት ነው ሥርአቱ
የት ነው አቤት የሚል ሕዝብ ሲደፈር መብቱ
ወያኔ ሰው ሲፈጅ ዘር እየቆጠረ በአያቱ በአባቱ።
ዓለም አቀፍ ያሉት የታል ፍርድ ቤቱ
ፍርድ ቤት ከሌለ ካልተሰማ እውነቱ
ጆሮ ዳባ ካለ ተሰምቶ ጩኽቱ
የተመድ ሽምድምድ አቅም የሌለው ነው፤
ጋሊ ድሮውንም ውሃ ውሃ የ የሚል የጥንት ጠላቴ ነው፤
የተመድ በውስጡ ሰው የለውሰው የለው
ዋይት ሃውዝ ድንጋይ ነው
ክሊንተንም ሰምቶ ሰማሁ የማይል ነው
ዋይት ሃውሰ በውስጡ ሰው የለው ሰው የለው
እኔ አቤት አልልም ለቢል ክሊንተን
አልለማመጥም ግብጻዊ ጋሊን
የተመድ ለአገሬ መፍትሄም አይሆን
ያገሬ ልጅ ተነስ እወቀው እቅጩን
አይቼዋለሁኝ የአፍሪካ የፈረንጁን
ያለኸው አንተነህ ትጥክህን አጥብቅ
ለነጻነታችን እንተናነቅ
ያገር ልጅ ቤልጅጌ ያገር ልጅ ምንሽር፤
ያገር ልጅ ጓንዶዬ አንጀቴን የሚያሽር፤
ያገር ልጅ ጠብመንጃ የአገር ልጅ አልቤን፤
ጠፍረህ አምጣልኝ አስረህ እጅ እጁን፤
አቶስታሹንና ቀጥቃጭ ቀጥቃጩን።




                                      









Monday, August 14, 2017

First Ethiopian-American Beer on the Go!



A remarkable and first of its kind, Ethiopian American Craft beer has been introduced last week to the American market here in the West Coast part of the United States. The beer is named “St. John” depicting the Ethiopian new year aka “Enqutatash.”


The St John Beer Produce was founded by a young and vibrant innovator, Alemayehu (aka Alex) Zenebe who recently came with the idea that America needs Ethiopian flavor in all parts of life. “It all started when I discovered the need for a beer that reflects a unique taste to blend with the already existing American hard cores such as Sam Adam. “Alex says.   As Ethiopian-Americans restaurants kept on growing across America,” continued Alex to say, “the need for a beer that reflects ‘a unique taste’ has been on upsurge creating a remarkable gap between high demand for a supply of smooth and flavored beers and hard and mass produced industrial classical beers. The Saint is discovered to feel this gap. The world is dynamic and changes are everywhere as time passes. We serve the needs of the new generation that is demanding change in the test of beer.” Alex stresses.
 St. John produced in two kinds, Premium Pale Ale and Premium Stout is a result of intensive research to offer a unique test. It is intended to compete and finally beat the dominant Netherlands’ Heineken light lager beer and the German’s lager “Beck’s.” We take advantage of our proximity to the American Market that enables us to supply freshly made beer than the imported European beers that lose their flavors on coming here passing through belligerent climatic conditions. The founder, says.
The new product is also a blessing to Ethiopians in the Diaspora who missed their home-made beer. “Compared to the imported Ethiopian Harrar, Meta and or the Eritrean Asmara beer, the Saint is by far the best” comments a beer vendor at Little Ethiopia, Los Angeles California. “For those of us in the Diaspora, a product like the St John beer is quite a blessing.” He added.
Local American beer drinkers also like the Saint according to Solomon Tamiru, a restaurant owner at Oakland. Customers who tasted St John beer increased their consumption and the Saint currently leads the number of sales in our restaurant beating the dominant Heineken and the Mexico produce, Corona.

“My son has been working his hands to the bones after perceiving the idea of changing the taste of beer and I am pleased the first batch is out in the market. I appeal to all Ethiopians and Americans drink the Saint and make my son rich. The Saint is out there to please. There is no need of importing beer for the Ethiopians in the Diaspora to drink.” His father Mr, Zenebe Tamirat said. "I witnessed his insistence and bravery while confronting hardship when he founded the "Ethiopian Basket Ball Federation in North America (EBFNA), while he was yet a college student. Today with MBA from a renown University, he has come with a credible innovation. He needs Ethiopian consumers buy the product.