Saturday, June 24, 2017

አማራ መደራጀት ጉዳይ/አቻምየለህ ታምሩ



”አገር ማለት በኢትዮጵያን አገላለጥ ከብሄር እስከ ጎጥ የሚካተት ጂኦግራፊያዊ ቦታ ነው። አንድ ሰው በተለምዶ የትውልድ ቦታ "አገሬ“ ሲል ይስተዋላል ወይንም ሊል ይችላል። አገርህ የት ነው? ጎንደር (ክ/ሃ)ወይንም ከዛ አሳንሶ ደብረ ታቦር እንዲሉበህግ ግን አገር ማለት አንድን ሰው ዚግነት ሰጥቶት የዜግነት መብቱን የሚያስከብርለት ባለመብቱም በዜግነቱ ግብር የሚገብርለት የጆግራፊ ቦታ ባለቤት አካል ነው። ኢትዮጵያውያን ዜግነታቸው የሚከበረው በኢትዮጵያ ነው። ስለዚህ የትውልድ ስፍfራቸው የትም ይሁን የት አገራቸው በህግ "ኢትዮጵያ“ ነች። በፖለቲካ ሳይንስ አተናተን አገር አገር ለመባል ማሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች አሉ። እዚያ ዝርዝር ውስጥ አልገባም። ነገር ግን ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥዋ ተለይቶና ታውቆ በተመድ የተረጋገጠላት አገር ነች። አማራ በኢትዮጵያ ክፍላተ ሃገራት ተሰራጭቶ የሚኖር ጎሳ ነው። ብዛቱና፡ በአገሪቱ ላይ ያለው የፖለቲካ ተጽእኖ እጅግ ሃያል ነው። ዜግነቱን የምታረጋግጥለት ”ኢትዮጵያ“ ስለሆነች አማራ ”ኢትዮጵያዊ“ ነው።“ (ተመዘዘ ስይፉ)


ReplyJust now


አማራ መደራጀት ጉዳይ
በአቻምየለህ ታምሩ
ከሰሞኑ የአማራው በአማራነት መደራጀት ጉዳይ እንደገና ተቀስቅሶ የውውይት አጀንዳ የሆነ ይመስላል። ገራሚው ነገር የአማራውን በአማራነት መደራጀት አጀንዳ እያደረጉ ያሉት ሰዎች በዘውግ ከተደራጁት ቡድኖች ጋር አብሎ ለመስራት ደፋ ቀና እያሉ ያሉ ግለሰቦች ጭምር መሆናቸው ነው። የአማራው በአማራነት መደራጀት ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም። ሆኖም ግን የአማራውን በአማራነት መደራጀትና «የአማራ ብሔርተኛነት» የሚባለውን የሌለ ነገር መለየት ያስፈልጋል። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ የአማራ ብሔርተኝነት የሚባል ነገር የለም። የአማራ ብሔርተኛነት ኢትዮጵያዊ ብሔርተኛነት ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ መኖር ያለበትና ሊኖር የሚገባው ኢትዮጵያዊ ብሔርተኛነት ብቻ ነው። ብሔር የግዕዝ ቃል ነው። ትርጉሙም አገር ማለት ነው። ብሔር የሚለው የግዕዝ ቃል ከህዝብ ጋር የሚያገናኝው ነገር የለም። ብሔር የሚገልጸው ምድሩን ነው። በእንግሊዝኛም ብሔር ማለት Nation ማለት ነው። United Nations የአገራት ህብረት ማለት ነው።
ያ ትውልድ ነገድን ብሔር ወይንም Nation የሚል ስያሜ ሰጥቶ ፖለቲካ ያካሄደው «ዳግማዊ ምኒልክ የተባለ የአማራ ንጉስ የተለያዩ አማራ ያልሆኑ «የአፍሪካ አገሮችን» ከኢምፔሪያሊስቶች ጋር በመመሳጠር ወርሮ በቅኝ ግዛትነት ይዟል» የሚለውን የትውልዱን የትግል መነሻ ጽንሰ ኃሳባዊ መሰረት ለመስጠት ነበር። በያ ትልውድ ፍልስፍና አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ሲዳማ፣ ሶማሌ፣ ወዘተ ብሔሮች ወይንም Nations ስለሆኑ የዛሬዋ ኢትዮጵያ የአገራት ህብረት ወይንም United Nations ናት ማለት ነው። በያ ትውልድ የፖለቲካ ትርጓሜ ኒዮርክ ባለው አለማቀፉ United Nations እና በUnited Nations [of Ethiopia] መካከል ልዩነት የለም።
ማንም ያድርገው ማን ብሔሮች ወይንም ብሔረሰቦች የሚባሉት ስብስቦች በነገዳቸው ዙሪያ የሚያደርጉት የብሔርተኛነት ትግል ጸረ ኢትዮጵያዊነት ነው። ይህ ጸረ ኢትዮጵያዊነት ትግል ወያኔ፣ ኦነግ፣ ኢሕአፓ፣ መኢሶን፣ ወዘተ የታገሉለት አይነት ትግል ነው። ወያኔ፣ ኦነግ፣ ኢሕአፓ፣ መኢሶን፣ ወዘተ የታገሉት ዋለልኝ በፈጠረው እስር ቤት ውስጥ የታጎሩት «ብሔር፣ ብሔረሰቦች»፤ ምኒልክ ከኢምፔሪያሊስቶች ጋር ተባብሮ አፍሪካን ሲቀራመት ከጠቀለለበት ኢትዮጵያ የምትባል እስር ቤት «ነጻ ወጥተው» ኦሮምያ፣ ትግራይ፣ ኦጋዴን፣ አፋር፣ሲዳማ፣ ወዘተ የሚባሉ አዳዲስ የምስራቅ አፍሪካ አገሮች እንዲመሰረቱ ነበር። የዚህ ትግል ግብ ነጻነት ወይንም እኩልነት አይደለም። እንዴውም ይህ ትግል ከነጻነትና እኩልነት ጋር አንዳች የሚያገናኘው ነገር የለም። በአካባቢያችን የተካሄደ የነገድ ብሔረኛነት እንግስቃሴ ግብ ምን ሊሆን እንደሚችል ማወቅ የሚሻ የወያኔ፣ የኢሕአፓ፣ የኦነግና የሻዕብያ ትግል ፍሬ ውጤት የሆነችዋን የኢሳያስ አፈወርቁዋን ኤርትራ ማየት ይችላል።
የያ ትውልድ ድርጅቶች እነ ወያኔ፣ ኦነግ፣ ኢሕአፓ፣ መኢሶን፣ ወዘተ የታገሉት የራሳቸውን ባንዲራ ፈጥረው፤ የክብር ዘብ አሰልፈው የህይወት ዘመን ፕሬዝደንት ሆነው የሚገዘግዙት አገር መፍጠር ነው እንጂ ትክክኛ የህዝብን የመብት፣ የመናገር፣ የመወከልና የንብረት መብት ነጻነት ለማምጣት አይደለም። ለዚህ ቢሆን ኖሮ የታገሉት በየለቱ ንግግራቸውና ተግባራቸው ሁሉ በራስ ሀብት ስለማዘዝ፣ ስለመናገር፣ ስለመወከልና ስለንብረት ማፍራት መብት ነጻነቶች ሲሰብኩ ይሰማና ይታይ ነበር።
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን «የኃሳብ ልዩነት የማያስተናግዱ ጨቋኝ» ብሎ ለነጻነት የታገለው ኦነግ ፋኖዎቹ የሚያነሱትን የኃሳብ ልዩነቶች መቀበል ተስኖት በቅድሚያ እነ ባሮ ቱምሳን ገደለ፤ ሲቀጥል ደግሞ እነ ሌንጮ ለታ አለን ያሉትን የሀሳብ ልዩነት ማስተናገድ አልችል ብሎ ሌንጮና በዙሪያው ያሉ ግለሰቦች ድርጅታቸውን ለማሻሻል ሀሳብ በማቅረባቸው የተነሳ ጠራርጎ በማባረር እነ ሌንጮ ለታ የኦነግ መሪዎች በነበሩበት ጊዜ እንደነ ጀኔራል ጃገማ ኬሎ አይነት ሀውልት ሊቀምላቸው የሚገባ የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያንን «ጎበናዎች» እያሉ ሲያሸማቅቁበት የነበረውን የኦነግ ስድብ ወደራሳቸው አዞሮ ትናንትና እነ ሌንጮ እነ ጀኔራል አበራ አበበንና መርዕድ መንገሻን «ጎበናዎች» እያሉ ሲያሸማቅቁበት በነበረው የኦነግ ስድብ ዛሬ በተራቸው እነሱን «ጎበናዎች» እያለ ሲሰድብ የሚውለው፤ አንድ የነበረው ኦነግ ግለሰቦች የተለየ ሀሳብ ባነሱ ቁጥር እየተሰነጠቀ ዛሬ ላይ ለስምንት ተከፍሎ በየሳምንቱ ጥምረት ሲመሠርትና ሽር ብትን ሲል የሚውለው፣ የኦሮሞን ገበሬ ከመሬቱ ሲያፈናቅል ከሚውለው የትግሬ አገዛዝ ጋር ምርጫ በደረሰ ቁጥር «እንደራደር እያሉ» አገር ቤት ለመግባት የወያኔን ደጅ የሚጠኑት እድሜ ልካቸውን የታገሉት እንደ መለስ ዜናዊ ጮሌ የሆነ አንዱ ኦነጋዊ የህይወት ዘመን ፕሬዝደንት ሆኖ የሚገዘገዘው የኦሮሞ አገር ለመመስረት እንጂ የሀሳብ ልዩነት ለሚከበርበት ነጻነትና የኦሮሞ ገበሬ የመሬት ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለመፍጠር ስላልነበረ ነው።
በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን የሀሳብ ልዩነት አልተከበረም ብለው የሀሳብ ልዩነት እንዲከበር ለመታገል ጫካ ገባን ያሉት ወያኔና ኢሕአፓም ልክ እንደ ኦነግ የታገሉት የራስ አገር ለመፍጠር እንጂ የሀሳብ ልዩነት እንዲከበር ወይንም ለነጻነት[for freedom] ቢሆን ኖሮ ወያኔ በየ አሥር ዓመቱ ለሁለት እየተከፈለ TAND, TPDM, ARENA, ወዘተ እያለ አይባዛም ነገር፤ ኢሕአፓም እንደ አሜባ ራሱን እየቆረጠ «ኢሕአፓ D» ምንትሴ እያለ እየተራበ እድሜ ልኩን ርስ በርስ ሲጫረስ አይኖርም ነበር።
ኢሕአፓ ከምስረታው ጀምሮ የታገለው ኢትዮጵያን በመበታተብ የዋለልኝ መኮነንን እስረኞች «ነጻ አውጥቶ» ከሰማኒያ በላይ የሚሆኑ አዳዲስ የአካባቢ አገራትን ለመመስረት ነበር። የኢሕአፓ አስተሳሰብ ውሉድ የሆነው ወያኔ ደግሞ ሻዕብያን ተከትሎ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ኢሕአፓ ሊመሰርታቸው የታገለላቸውን ከሰማኒያ በላይ በየነ መንግስታት ወደ ዘጠኝ ክልሎች በማጠፍ የትግራይን የበላይነት በሌሎችን ኢትዮጵያውያን ፍዳና መከራ ላይ ማደላደል እስከቻለ ድረስ እንዳሻው የሚያስገብራት፤ ነገር ግን በማንኛውም ጊዜ ዘጠኝ አገር ልትሆን የምትችል የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ስብስብ ፈጠረ። የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ ወዘተ ብሔርተኛነት የወለደው ትግል አሁን ያጋመስነው እንደ ሕዝብ የመኖር እጣችን ለጊዜውም ቢሆን ጥያቄ ውስጥ የሚገባበት አሊያም የሚያቆምበት ደረጃ ላይ አድርሶናል። አማራው በታሪኩና በባህሉ ጥላቻ ስለሌለው የነ ኦነግ፣ ወያኔ፣ኢሕአፓና ወዘተ አይነት ደም የተጠሙ ድርጅቶች ትግል አያደርግም።
ከዚህ በፊት እንደተናገርሁት የአማራ ክልል ኢትዮጵያ ነች። የኦሮሞም ሆነ የሌሎች የኢትዮጵያ ነገዶች ክልላቸው ኢትዮጵያ ናት። አማራው የሚያደርገው ትግል በዚች በክልሉ በኢትዮጵያ ከሌሎች እኩል በጋራ ለመኖር ነው። የአማራ ብሔርተኛነት የመፍጠር ሕልም ይዞ ወያኔና ኦነግን መውቀስ ግብዝነት ነው። ትክክለኛው የፖለቲካ ትግል ሁሉም ኢትዮጵያውያን ማንነታቸውና ኃይማኖታቸው ተከብሮ፤ ቋንቋቸውን እየተናገሩ በዜግነት እኩል ሆነው የሚኖሩበትን አገር የመፍጠር እንቅስቅሴ ነው። ይህ አይነት ትግል ከነገድ ብሔርተኛነትጋር የሚያገናኝው ነገር የለም።
የሆነው ሆኖ አማራ እያካሄደው ያለው ትግል በሰፊዋ አገሩ በዜግነት እኩል ሆኖ ለመኖር የሚያካሄድ ተጋድሎ ወይንም የኢትዮጵያ ብሔርተኝነት ትግል እንጂ የአማራ ብሔር ወይንም Amhara nation ለመፍጠር አይደለም። የአማራ ብሔር ኢትዮጵያ ነች። የአማራ ወይንም የኦሮሞ ብሔርተኝነት የሚባለው እንቅስቃሴ ኢትዮጵያን አፍርሶ በሸምበቆ አጥር ተከልለው ርስ በርስ የሚተረማመሱ የአካባቢ መንግስታትን የመመስረት ጸረ ኢትዮጵያ ትግል ነው። ባጭሩ አማራ ከፍ ብለን እንዳየነው አይነት የከሰረ ትውልድ የነገድ ብሔርተኛነትን የትግል መመሪያው አድርጎ ትግል አያካሂድም።
ማንበብ ከብዙ ስህተት ያድናል። ባሌ ከጥንት ጀምሮ የአማራ ጭምር ርስተ ምድር የነበረ፤ ግራኝ አህመድ «የባሌ አበሾች ሰይጣኖች ናቸው» ሲል የመከሰረላቸው የባሌ ነጋሹ የራስ ተክለ ሃይማኖት ግዛትና ከግራኝ አህመድ ጋር ሲዋጉ ለአገራቸውና ለኃይማኖታቸው የወደቁት የባሌ ተወላጆች የነ ራስ ነብያንትና የነ አዛዥ ፋኑኤል መቃብር ነው። ደዋሮ [የዛሬው ምዕራብ ሐረርጌ] የልብነ ድንግል የጦር አዝማች የነበረው የቢትወደድ በድል ሰገድ ርስት ነው። ዳሞትና ቢዛሞ[የዛሬው ወለጋ] በሽምግልና እድሜው ግራኝን ለመፋለም ዘምቶ አስደማሚ ተጋድሎ ያደረገው የልብነ ድንግል የጦር አዛዥ የአዛውንቱ የራስ ወሰን ሰገድና የጀግናው ልጁ የባህር ሰገድ እትብት የተቀበረበት አገራችን ነው። ፈጠጋር[ የዛሬው አርሲ] እነ ነጋሽ ተክለ ሐዋርያት ከግራኝ ጋር ሲፋለሙ የወደቁበት ያያቶቻችን ርስት ነው።
ስለዚህ አማራው የሚጋደለው በአባቶቹ አገር በኢትዮጵያ እኩል ዜጋ ሆኖ ለመኖር እንጂ እንደ ወያኔና ኦነግ ለብሔርተኛነት አይደለም። ብዙ ሰው የአማራው በአማራነት መደራጀት ለወያኔ ስኬት ነው ብሎ ያስባል። ይህ በጣም የተሳሳተ ነው። አማራው በኢትዮጵያ ለመኖር የሚያደርገው ትግል የወያኔ ስኬት ሊሆን አይችልም። የአማራው በአማራነቱ መደራጀቱ የወያኔ ስኬት የሚሆነው የአማራው ትግል የአማራ ብሔርተኛነት ከሆነ ነው። አማራው ለብሔርተኛነት ከታገለ የሚታገለው ለኢትዮጵያ ብሔርተኛነት ነው።
አቻምየለህ ታምሩ
9 Comments
Comments
ድል ለአማራ ህዝብ አቻምየለህ ይህን ቢፅፍ ምንም አይደለም ከየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አስተሳሰብ ውጪ እንደመሆኑ በግለሰብ አቋምነት ስለሚያዝለት ከፅሁፉ ጋር መስማማት ወይም አለመስማማት ይቻል ይሆናል እንጂ ሌላ ተያያዥ ጉዳዮች ላይኖሩ ይችላል አቶ አንተነህ ግን የአማራ ብሄርተኛ ድርጅት አባልና አመራር ሆነህ ሳለ የአማራ ብሄርተኝነት የለም ካለም የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ነው… የሚልን ፅሁፍ ስታጋራን ምን ያህል ፖለቲካዊ አቋምህ እንደዋዥቀ ወይም ሲጀመርም ፖለቲካዊ አቋም እንደሌለህ አሳባቂ ነው። ሌላውን ለጊዜው ልተወውና የአማራ ብሄርተኝነት የለም ያለው ኢትዮጵያዊ… … ነው ብለህ ካመንክ ወይም ከተስማማህ ማንነትን መሰረት አድርጎ በተደራጀ ድርጅት ውስጥ ምን ታደርጋለህ? ጊዜህንና ጉልበትህን ስለምን ባላመንክበት የትግል መንገድ ታፈሳለህ? ያለው የኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ከሆነ ለምን በአንድነት ጎራው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ተሰልፈህ አትታገልም? ቦታህን ያወቅህ አልመሰለኝም ብሄርተኛ ያልሆነ አማራ በአማራ ብሄርተኝነት ትግል ውስጥ ቦታ የለውም!!!!

Reply
9
June 22 at 4:44pm
ፅናቱ አማረ በዛም በዚህም ብየ ልረዳው ከምን አንፃር ብሄርተኛ እሚባል ነገር የለም እነዳለ ላየው ብሞክርም ሊገባኝ አልቻለም።የአማራ ብሄርተኝነት የለም የኦሮሞም የለም የኢትዮጵያ ግን አለ ማለት ምን እሚሉት ትርጓሜ ይሰጠው?? አንድን ጎሳ ብሄር ካላልን ምን እንበለው የኢትዮ ብሄርተኝነት ታዲያ እንዴት ኖረ በዚህ ትርጓሜ።ወይ እንደ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ብሄር ማለት ቋንቋ ነው እኔ አማራ ነኝ ኦሮሞ ነኝ ማለት ቋንቋየን ነኝ ማለት ነው ይበለን በዛ በኩል እንረዳ።ለማንኛውም እጅግ ይረደ ሊፈታ ሊተረጎም የማይችል እጅ እና እግር የለለው ፅሁፍ ነው ለኔ በግሌ አልገባኝ ሊሆን ይችላል የተረዳውት ግን እንደዛ ነው።

Reply
1
June 22 at 5:18pm
Temezeze Seifu "ጎሳ" tribe ነው “ ለምሳሌ “አማራ” ጎሳ ነው "ብሄር” አገር ነው ለምሳሌ ኢትዮጵያ አገር ናት በእንግሊዘኛው State, Country ወይንም Nation ልትባል ትችላለች

Reply1 hr
ፅናቱ አማረ ሀሀ ሰለዚህ 87 አገር አሉን ማለት ነው በኢትዮጵያ 😃?

Reply9 mins
ምኒልክ የአንጎለላ ዕንቁ ሰው አሁን እዚህ ላይ መኮመት እችላለው በነፃነት።
በመጀመርያ የአማራን መደራጀት በመቀበሉና ይህንንም ባዳባባይ በመናገሩ ላመሰግነው አወዳለው በመቀጠል ግን እኔ የአማራ ብሔርተኝነት የለም የሚለው አስተሳሰብ አማራ የለም ከሚለው አስተሳሰብ ጋር አንድ አይነት ሆነብኝ እና ግር አለኝ በዚህ ፅሁፍ ውስጥ እርስ በእርሳቸው የሚጣሉ አስተሳሰቦች ይታያሉ።
፦የአማራ መደራጀት ለምን? 

፦ብሔር ሀገር ማለት ነው ይለናል ልክ ነው ግን ሀገር ማለት እራሱ ምን ማለት ነው?
፦አንድ ህዝብ ሀገር አለኝ ወይም ይህ አገር የኔ ነው ለማለት የሚችለው ምን ሲሟላለት ነው?
፦አማራው በዚህ ሰአት በእርግጥ ሀገር አለው?
እነዚህ ጥያቄዎች ምናልባት ቢመለሱልን ደስተኛ እሆናለው።
ሌላው በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ያየሁት የተንሸዋረረ እይታ የአማራን አደረጃጀት ወይም እንቅስቃሴ ከሌች ጋር ማነፃፃሩ ነው አማራ የራሱ በቂ የሆኑ ምክንያቶች እያሉትና ከራሱ ምክንይልት አንፃር መተንተን ሲገባ ከሌች እንቅስቃሴ ጋር በማስተያየት ለመተንተን መሞከሩ ስህተት ነው አማራ ማንንም አይቶ ወይም ከማንም ኮርጆ ይህን እንቅስቃሴ አልጀመረም።

Reply
3
June 22 at 6:46pm
Temezeze Seifu አገር ማለት በኢትዮጵያን አገላለጥ ከብሄር እስከ ጎጥ የሚካተት ጂኦግራፊያዊ ቦታ ነው። አንድ ሰው በተለምዶ የትውልድ ቦታውን "አገሬ“ ሲል ይስተዋላል ወይንም ሊል ይችላል። አገርህ የት ነው? go

Reply49 mins
Temezeze Seifu አገር ማለት በኢትዮጵያን አገላለጥ ከብሄር እስከ ጎጥ የሚካተት ጂኦግራፊያዊ ቦታ ነው። አንድ ሰው በተለምዶ የትውልድ ቦታውን "አገሬ“ ሲል ይስተዋላል ወይንም ሊል ይችላል። አገርህ የት ነው? ጎንደር (ክ/ሃ)ወይንም ከዛ አሳንሶ ደብረ ታቦር እንዲሉ። በህግ ግን አገር ማለት አንድን ሰው ዚግነት ሰጥቶት የዜግነት መብቱን የሚያስከብርለት ባለመብቱም በዜግነቱ ግብር የሚገብርለት የጆግራፊ ቦታ ባለቤት አካል ነው። ኢትዮጵያውያን ዜግነታቸው የሚከበረው በኢትዮጵያ ነው። ስለዚህ የትውልድ ስፍfራቸው የትም ይሁን የት አገራቸው በህግ "ኢትዮጵያ“ ነች። በፖለቲካ ሳይንስ አተናተን አገር አገር ለመባል ማሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች አሉ። እዚያ ዝርዝር ውስጥ አልገባም። ነገር ግን ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥዋ ተለይቶና ታውቆ በተመድ የተረጋገጠላት አገር ነች። አማራ በኢትዮጵያ ክፍላተ ሃገራት ተሰራጭቶ የሚኖር ጎሳ ነው። ብዛቱና፡ በአገሪቱ ላይ ያለው የፖለቲካ ተጽእኖ እጅግ ሃያል ነው። ዜግነቱን የምታረጋግጥለት ”ኢትዮጵያ“ ስለሆነች አማራ ”ኢትዮጵያዊ“ ነው።

ReplyJust now
Anteneh Mulugeta በአማራነት ስለመደራጀት እና ኢትዮጵያዊነት

ሰሞኑን አንዳንድ የአማራው ትግል መሪዎች: አክቲቢስቶችና ጋዜጠኞች "ብአዴንን አትንኩብን" የሚል ውትወታ በሶሻል ሚዲያው ተደጋግሞ ስለታየ ብዙ ሰዎች የአማራ ድርጅቶች ወዴት እየሄዱ ነው? የሚል ጥያቄ እያቀረቡልኝ ነው:: 
...See More

Reply
2
June 22 at 7:33pm
ምኒልክ የአንጎለላ ዕንቁ ሰው አሁን አንተ በምትለን መልኩ ከሆነ የአማራን ትግል ወይም ብሔርተኝነት አትቀበልም ማለት ነው? ትንሽ ግር ስላለኝ ነው የአማራን ብሔርተኝነት ትግል የተረዳከው እንደ ሀገር አፍራሽ ነው ማለት ነው? አንተ ያለህበት ድርጅት ስለ አማራ ብሔርተኝነት ምን ይላል? AntenehMulugeta
አከለው አማራ አንድ የጎንደር አማራ ወጣት አንድ የባህር ዳር አማራ ወጣት ብትጠይቀው እነሱ ጋር አልኖርም ይልሀል።አንተነህ ከግንቦት ነው የመጣው አትፍረዱበት የሚበላ እንጅ የማይሰራ ድርጅት።
Dawit Tibebu አቶ አንተነህ ሁል ግዜ የአንድነቱ ሃይል በተናጋ ቁጥር ወቅት እየጠበቅህ እንደዚህ አይነት ነገሮችን ትፅፋለህ የተወሰኑት ጓዶችህም እንደዛው እስኪ አባት አገር አማራን እንመሰርት አለን ከሚሉት ውስጥ ብአዴንን አትንኩ ያሉ በስም አንድ ግለሰብ ጥራልን ?ሌላው ድርጅታችን ሁለት ነገሮችን ይዞ ይንቀሳቀሳል ብላችሁን ነበር ።
1/ፕላን A አማራው በአማራነቱ ተደራጅቶ በኢትዮጵያ መአቀፍ ሲሆን 2/ፕላን B 
...See More

Reply
2
June 22 at 9:14pmEdited
Begemdr Amhara ብአዴንን አትንኩብን የሚሉት ሰዎች እኮ ከቤተ አማራ ከድተዉ ከእናተ ጋር የተዋሃዱት ግለሰቦች እንጂ የአማራ ነፃ መንግስት እመሰርታለሁ የምትለዋ የትክክለኛዋ የቤተአማራ አባላትና አመራሮች አይደሉም ፡፡

Reply
1
June 22 at 9:51pm
Temezeze Seifu ውድ አቶ አንተነህ ሙሉጌታ የአማራን አደረጃጀት በተነሳ ያስቀመጥከው አንጀቴን አርሶታል እግዚአብሄር ይስጥህ። ስለ ሌላው አሳብህ መቼም ብትደውልልኝ ደግ ነው። አማራዊ ጥበብ ያስፈልገዋልና። የውይይቱን መነሻ የጻፈው ወንድማችን ስለ ብሄር ትርጉም የ1966 ፖለቲከኞች የሰጡት ትርጉም አሳሳች መሆኑን በተለይም ዋለለኝ ገና ትምህርቱን ሳይጨርስ ስለ ብሄር የሰጠው ኧትርጉዋሜ ሰፊውን ስእል የማያሳይና አባታችን ተስፋ ገብረስላሴ “ዘ ብሄረ ቡልጋ” እያሉ በፊደል መማሪያችን ላይ ይጽፉት በነበረው ላይ የተመሰረተ ይመስላል። የሚያሳዝነው የ 1966 ኮሚኒስቶችና ምሁራኖቻቸው ስህተቱን ተቀብለው በዚያው መንጎዳቸው ነው። አለበለዚያ የአቻሚለህ ትርጉም ከሰፊው ስእል እይታ ትክክል ነው። ስለዚህ ጉዳይ በአንድ የሳይበር ውይይት ላይ (6 አመት ገደማ ይሆናል) ተነስቶ ብሄር፤ አገር ጎጥና የመሳሰሉትን ትርጉማቸውን በመስጠት ምሁራን እንዲተቹበትና የዋለለኝ ስህተት እንዲታረም ያቀረብኩት 25 ገጽ ገደማ የሆነ ጽሁፍ ስላለ ይህን ጽሁፍ በግርድፉ አይተው ለመሰለቅና ለማስተካክል ወይንም ሃሳባቸውን ለመስጠት ለሚፈልጉ ማስተላለፍ እችላለሁ። አንተነህ የጠቀስከው የፕ/ር አስራት ሞዴል ዛሬ እኔ “አማራነት በኢትዮጵያዊነት" (The Amhara within") በሚል (የመአህድ ፖሊቲካል ቲዎሪ)የምሟገትበት ነው። ይህን ሞዴል የአንተ ሞዴል ማድረግህ አስደስቶኛል። ይህን ሞዴል ወስደን ያልተከፋፈለና የታጠቀ ጠንካራ የአማራ ሃይል በኢትዮጵያ ብሄረተኝነት ብናደራጅና ሁላችንም ብንረባረብ ወያኔ ባጭር ጊዜ ይጠፋል

Reply
1
Yesterday at 6:32pm
ምኒልክ የአንጎለላ ዕንቁ ሰው AntenehMulugeta ይህ የዶክተር ሰማኸኝ ጋሹን ትንታኔ እንዴት ታየዋለህ የህግ ምሁር እንደሆንክ እናውቃለን እሱም እንዳንተው የእግ ምሁር ነው 

ወንድማችን አቻሜለህ አንድ የሚያወያይ ሃሰብ ሰንዝሮአል። የአማራው በአማራነት መደራጀት ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም ካለ በሗላ የአማራ ብሔርተኝነት የሚባል ነገር የለም የአማራ ብሔርተኛነት ኢትዮጵያዊ ብሔርተኛነት እንደሆነ ገልጿል። በእንግሊ
...See More

Reply
1
June 22 at 9:20pmEdited
Tegegne Teshome I hope the issue is against the ideology of Bete Amhara not against other amhara political parties.
ኃያል ሰው አማራ ለማንነቱ ሲሰባሰብ፣ ለህልውናው ሲደራጅ ምነው ጫጫታው በረከተ? የአማራን ብሔርተኝነትን የለም ለማለትና ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነት ለማለት ለምን ተፈለገ? እውነት ሁሌም መራራ ልትሆን ትችላለች፣ እውነትን መቀበል ደግሞ አእምሮ ላለው ዜጋ ዋና ነገር ነው። እናንተ አማራው በግፍ በትር ሲቀጠቀጥ፣ ሲፈናቀል፣ ሲዋረድ፣ ሲታሰርና ሲገደል ድምፃችሁ ያልተሰማው ሲደራጅ ለመበታተን ያዙኝ ልቀቁኝ የምትሉት። አማራ ግን ወደ ኋላ ላይመለስ ወደ ፊት ጉዞ ጀምሯል። ነባራዊው እውነት ይህ ነው።

Reply
1
June 22 at 11:04pm
Kibrom Gedey It is agood analysis Acham go ahead
Makbel Dawit የ ፕ / ሮ ፍቅሬ ቶሎሳ አይነት፤ ገራገር ጹሁፍ ነው ማለት ይችላል ። በተለይ አንዳንዶች ገባ ብለን እንተንትን ብንል ፣ አስደንጋጭ ውጤት ነው የሚሰጡ ። ለማንኛውም አቻምየለህ የምወደውና የማደንቀው ልጅ ነው ። ባለህበት ሠላም ሁንልኝ ።

No comments:

Post a Comment