Monday, June 26, 2017

የክቡር ፕሮፌሰር አስራት አጽም ወደ ቅድስት ስላሴ መካነ መቃብር በክብር ተዘዋወረ


በወያኔ እብሪትና እምቢ ባይነት የዛሬ 18 ዓመት አስከሬናቸው በቅድስት ስላሴ መካነ መቃብር እንዳያርፍተከልክሎ ባለወልድ ቤ/ክ አርፎ የነበረው የክቡር ፕሮፌሰር አስራት አጽም ዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2009 ዓ/ም በክብር ተነስቶ ወደ ሚገባው ሥፍራ ወደ ቅድስት ስላሴ መካነ መቃብር በክብር ተዘዋወረ። 
የተለያዩ የትግሬ ነጻ አውጭ ፓርቲ ተቃዋሚ አባላት በተለይም የአንድነት ኃይላትና ፕ/ሩ የመሰረቱት የመአሕድ አባላት፤ የፕ/ሩ ቤተሰቦችና ወዳጆች እንዲሁም አያሌ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት በዚህ ስነሥርአት የክቡርነታቸው የሕይወት ታሪክ የተነበበ ሲሆን ስርዐተ ፍታትም ተፈጽሟል። በመጨረሻም አሰከሬኑ በታላቅ አጀብ ታጅቦ የነጻነት ሃውልትን ከዞረ በኋላ ቅድስት ሥላሴ መካነ መቃብር በክብር አርፏል።

ክቡር ፕ/ር አስራት ወልደየስ በሽግግር መንግሥት ምስረታ ላይ ወያኔ ኤርትራን ሲያስገነጥል ብቸኛ ተቃዋሚና ያ ጉባኤ በኤርትራ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት የሞራልም ሆነ የሕግ ሥልጣን እንደሌለው ማንንም ሳይፈሩ በግልጽ ያስጠነቀቁ ጀግና ነበሩ።
ፕ/ር አስራት አማራው ባልተሳተፈበት የሽግግር መንግሥት መመስረቱ የቆረቆራቸው ወገኖቻቸው ያደረጉላቸውን ጥሪ በመቀበል የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅትን አብረው በመመሥረትና ግንባር ቀደም መሪ በመሆን ለዐማራው ሕልውና ሲታገሉ ወያኔ የተለያዩ ሰንካላ ምክንያቶች በመፍጠር ወህኔ ካዋላቸው በኋላ በማንገላታትና ሕክምና በመከልከል ጥፋተኛ ነኝ ብለውና ይቅርታ ጠይቀው ከእስር እንዲለቀቁ ቢያባብላቸውም ”አገር ጠባቂ ወያኔ አገር በዳይ አስራት” 'ይህ እንዴት ይሆናል?' በማለለት ሃሰትን ከመቀበል እውነትን ይዞ ለአገር መሞትን መርጠው ግንቦት 8 ቀን 1991 ዓ/ም ተሰውተዋል።
ፕ/ሩ የወሰዱት አቅዋም እንደ አባቶታቸው እንደ አጼ ቴዎድረስና እንደ አቡነ ጴጥሮስ ከሰማእታት ጎራ ቢያስቆጥራቸውም በድርጅታቸው ዙሪያ ሰፍሮ የነበረውን ወጣት ያንገበገበና ያስቆጣ በመሆኑ "አንድ አስራት ቢሞት ሺ አስራቶች ተፈልፍለናል“ በማለት የወያኔን ሞት በማቃረብ ደማቸውን ለመበቀል የሞት የሽረት ትግል በማካሄድ  ላይ ይገኛሉ።
አስራት ሕያው ነው!
የአስራት ልጆች ተባበሩ!
ሞት ለወያኔ!



                      

No comments:

Post a Comment