ታንከ በሕዝባዊ ቁጣ ላይ አይሰራም
ከዘነበ ታምራት
የፊታችን ቅዳሜ ባሕርዳር ሊደረግ የታቀደውን ሕዝባዊ ስብስባ ለማኮላሸት የትግራይ
ነጻ አውጭ ግንባር ባዶ እጁን የሚወጣውን ሰላማዊ ሰልፈኛን በታንክ ለመበተን እየተዘጋጀ መሆኑን ፌስቡክ ላይ አነበብኩ። ወያኔ በ
1997 አዲስ አበባ ላይ በተደረገ ሕዝባዊ አመጽ ታንክ አውጥቶ ሕዝብን ለመፍጀት መቃጣቱ የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አገሪቱን ከጠላት ለመከላከል በገዛው ከባድ የጦር መሳሪያ ራሱ ሊደመሰስበት
አፈ ሙዝ የዞረበት ለመጀመሪያ ጊዜ በወያኔ ነው። አሁንም በባሕርዳር ሕዝባዊ ስብሰባ ወያኔ እንደለመደው እንኳን ታንከ ኒውክሌር
ቢያወጣ ጀግናው የአማራ ሕዝብ የሚበገር እንደማይሆን ወያኔ ተረድቶ ከድርጊቱ መቆጠብ አለበት። ይህ ባይሆን ግን ጸረ ሕዝብ የሆነውን
ትእዛዝ የሰጠው ባለ ስልጣን ወየውለት። ማርያምን፤ የአማራው ሕዝብ አይምረውም! በ 1997ቱም ጊዜ ለወጣው
ታንክ ትእዛዝ የስጠው ራሱ መለስ ዜናዊ እንደነበር ታውቋል። ይህም ወንጀለኛ ከእግዚአብሄር ፍርዱን አግኝቷል። ተባባሪዎቹም የታወቁ
ስለሆኑ ፍርዳቸውን ለመቀበል ጊዜያቸውን እየጠበቁ ናቸው። እነዚህ ልባቸው የተደፈነ ወያኔዎች ሕዝብን ከመጤፍ ባለመቁጠር የፈጸሙት
ግፍ የሁዋላ ኋላ ራሳቸው ላይ እንደሚጠመጠም ልብ አይሉም።
በሰላማዊ ሰልፍ ላይ በተገኙ ዜጎች ላይ ታንክ በመደገንና በመግደል እስከ ዛሬ የሚታወቁ
የለየላቸው ጸረ ሕዝብ መንግስታት ቻይና፤ ሶርያና በትግራይ ወያኔ ግንባር የሚመራው የኢትዮጵያ መንግሰት ናቸው። የ 1989ኙ የቴናነም አደባባዩ እልቂት
በስልጣን ሽኩቻ የተወጠሩት የቻይና አምባገነኖች መሪዎች ውጤት ነው።
በቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ወሰን የለሽ ስልጣን ሲረገጥ የነበረው የቻይና ሕዝብ በተለይም ወጣቱ ክፍል የዲሞክራሲ አመራርን በመጠየቅ
ለአሰርተ አመታት ስላማዊ ሰልፍ በመውጣት አያሌ አቤቱታዎችን ቢያቀርብም ከመታሰርና በየምክንያቱ እየታፈነ ከመገደል አልዳነም። በተለይም
በ 1987 /ም የቴይናነም አደባባይን ባጥለቀለቀው
ሰልፍ 24 ወጣቶች በመታሰራቸው ወዲያውንም ነጻነተኛ /ሊበራል ናቸው ተብለው ይታሰቡ የነበሩትና የተማሪውን ንቅናቄ ይደግፉ የነበሩት
የፓርቲው ዋና ጸሃፊ ሁ ያቦንግ ስልጣናቸውን
ቢለቁም በፓርቲው ባለስልጣናት መካክል በነበረው ሽኩቻ ሸር በመገደላቸው የሕዝብ ቁጣ አገንፍሎ ቴያናምነን አደባባይ እንደገና በሕዝብ
ቁጥጥር ሰር ዋለ። ሕዝብ ተማማለ። የኮሚኒስት ፓርቲው ሰልጣኑን ዲሞክራሲያዊ
ካላደረገ ቤቴ አልመለስም አለ።የኮሚኒስቱ ፓርቲውም ይፈርሳል ተብሎ ተፈራ።
ይሁን እንጂ በዚህ መሃል አክራሪው ኮሚኒስት
ዜንግ ዚኦፒንግ ሽኩቻውን ጥስው ወጥተው የፓርቲው ዋና ጸሃፊ ሆነው አድፍጠው ቁጭ ብለው ኖሯል። አምባገነኑ ኮሚኒስት ፓርቲው ሕዝባዊ
አመጹን በሃይል ከመደምሰስ ሌላ አማራጭ የለም ሲል አወጀ። ቀጥሎም በቀላል ብረት ለበስ የታገዘ ሃይል ወደ አስፈሪው ቲያናምነን
አደባባይ ላከ። ሆኖም ይሄ ኃይል ሕዝቡን የፈራ መስሎ ምንም ጉዳት ሳያደርስ ተመለሰ። ይህም ለአንዴና ለመጨረሻው ሕዝባዊ አመጹን
ለመጨፍለቅ ሆን ተብሎ የታቀደ ነው ይባላል። እንደተባለውም ኮሚኒስት ፓርቲው ለሕዝቡ ጥያቄ ዲሞክራሲያዊ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ
በከባድ ብረት ለበስ የታገዘ ጦር ልኮ በገዛ ወገኑ ላይ ዘመተ። በቲይናምነን
አደባባይ መሬት ሲኦል ሆነች። ለጠላት የተመረቱ ታንኮችና ብረት ለበስ የጦር መሳሪያዎች አፈ ሙዛቸውን ወደ ወገን አዞሩ። ለአምባገነን
መሪዎች ቆሙ። የሕዝብ ልጆች በጥይት ተጨፈጨፉ፤ በታንክ ተጨፈለቁ።
በሌላ በኩል ታጋዮች ዝም ብለው አልተሰውም።
ከዘላለም ባርነት የአንድ ቀን ነጻነትን መርጠው ጠላትን እየጣሉ ወደቁ። አያሌ ታንኮችንና ብረት ለበስ ተሽካሪዎችን አቃጠሉ። አያሌ
ወታደሮችን እያነቁ ወደቁ። እስካሁንም ድረስ አርማቸውን አንስተው በቻይና ለዲሞክራሲ የሚታገሉ አሉ። ቻይናም በነዚህ ታጋዮች ደም ተገነባች። የዓለም ታላቅ የኢኮኖሚ ኃይልም ለመሆን
በቃች።“ታጋይ ይሞታል እንጅ ትግል አይሞትም።” የሚባለው ለዚህ ነው።
ካለ ሞት ስርየት የለም። ጥቂት ልጆቿ ሞቱ፤ ቻይና ግን ዳነች።
የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባርና አሽከሮቻቸው
የአማራ፤ የኦሮሞና የደቡብ አሳፋሪ አሰካሪዎች የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን ልምድ ይወስዱ ይሆናል። ጎንደር ላይ የፈሩ መስለው መመለሳቸው
የቲያናምነን አደባባዩን ሕዝባዊ አመጽ ለማክሸፍ ከተላከው የቻይና ኃይል አሰራር ጋር ይመሳሰላል። የባሕርዳሩ በታንክ የተጠናከረ
ከሆነ ከፍተኛ መስዋእትነት ሊጠይቅ ስለሚችል ከወዲሁ መታጠቅና ለፍልሚያው መዘጋጀት ያስፈልጋል። በተለይም አማራ የሆንክ በማንኛውም
ጊዜ አገርህን ያገለገልክ ወይንም አሁንም በመከላከያ ሰራዊት ያለህ ትግሬ ያልሆንክ የሰራዊቱ አባል ሁሉ የወያኔን ጭፍጨፋ ለማክሸፍና
ወገንን ለመታደግ ቆርጠህ ተነሳ። ታንክ ማስፈራሪያ ሊሆን ይችል ይሆናል እንጂ በሕዝባዊ ቁጣ ላይ አይሰራም።
ነጻነትክን እንደዋዛ የተቀማህ ወገኔ ሆይ! ተነስ! ማን ይፈራል ሞት?ማን ይፈራል? ለአገር ለወገን ሲባል፤ ሁሉም ሰው ይሞታል!እያልክ ዘምር!
ጸሃፊው ዘነበ ታምራት በስልክ ቁጥር 310 774 6007 ይገኛሉ።
Follow
@Neguodguadzeneb
No comments:
Post a Comment