Thursday, May 19, 2016

የዛሬይቱ ኢትዮጵያ እውነተኛ ገጽታ!





ከህሊና ወንድይራድ

አገራችን ኢትዮጵያ ብዙ  ሺ ዘመናት አኩሪ ታሪክ ባለቤት ሐገር እንዳልነበረች ዛሬ በባንዳ ርዝራዦች መዳፍ ሥር ወድቃ የባለመቶ አመት ባለታሪክ ተብላላች።በጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን ደምና አጥንት የጸናች ምድር የተባዮች መፈንጫም ሆናለች።

*የአገር  ባለውለታ የሆኑ አርበኞቿ ሜዳ ላይ ወድቀው ሲያደሟትና ሲያዳክሟት የኖሩ ዛሬ ላይ ተንደላቀው የሚኖሩባት
 “ኢትዮጵያ ሐገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ፣
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ።”
የሚለው ዜማ ዛሬም ትኩስ ሆኖ የሚደመጥባት ብቸኛዋ ምድር የኛዎ እማማ ኢትዮጵያ ሆናለች።
በትግራይ ወያኔ አገዛዝ የወደቀችው አገራችን ሕዝቧ ዘላለማዊው አምላክ የለገሰውን ነፃነት ተነጥቆ በባርነት የሚማቅቅባት፣ዜጎቿ በረሃብ የሚረግፉባት፣ በበሽታ የሚሰቃዩባትና ተፋ የጨነገፈባት የጥቂት ወሮበሎች  ሐገር ሆነች።
የትግራይ ወያኔዎችና ግብረ አበሮቻቸው ተምረው የተመረቁ ወጣቶችን ድንጋይ ጠራቢ በማድረግ የምትኩራራና በአደባባይ የምትደሰኩር ሃፍረተ-አልባ ገዢዎች የሚዘውሯት የፍርደ ገምድሎች ርስተ ጉልት አደረጓት።
ይማኖት አባቶቿን  አሰድዳ እያንከራተተች በካድሬ የቀበሮ ባህታዊያን ቤተመቅደሷን ያስወረረች  መንፈሳዊነትና ህሊና በሌላቸው የአስመሳይ ካህናትና ፓስተሮች መነገጃ የገበያ ማዕከል የሆነች ሐገር ሆነች።
አንድ ሆኖ ወራሪን አይቀጡ ቅጣት የቀጣ፣ለጥቁር ሕዝቦች ፋና ወጊ የሆነ ሕብረብሄራዊ ሕዝቧን በወንዝና በመንደር የሚከፋፍሉና የሚያናክሱ መርዛም ኮብራ እባቦች የበቀሉባት ኪነ-ጥበቧ በሃሰት ተሽሞንሙኖ የሚቀርባትና ዕውነት የቀጨጨባት፣አሰመሳይነትና አደባይነት የነገሰባት ሲኦላዊ ምድር ልትሆን አበቋት።
ዛሬ ያላቅሟ የምትንጠራራ ከሰራችው ይልቅ የምታወራው የሚበዛ በሃሰት ሚዲያ የደነቆረች የሆዳም ጋዜጠኞች መፈልፈያ፣ የእውነተኛ ጋዜጠኞች መሰቃያ ምድር ኢትዮጵያ ናት።
ዛሬ ባልተማሩ የምትመራ ለነፃነቷ የሚታገሉ ልጆቿን በሰቆቃዊ ስፍራ አጉራ የምታሰቃይ ምድራዊ ገሃነም ኢትዮጵያ ናት።
የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ከላይ የተዘረዘሩትን እውነታዎች አታሟላም የሚሉ ካሉ ህሊናቸው ያልተሟላ ወይም በጥቅም የታወረና ሞራላቸው የላላና ከገዢዎች ጋር የሚቆምሩ የበግ ለምድ የደረቡ ተኩላዎች መሆን አለባቸው።
ኢትዮጵያ በጠላት ዘመን ይህን ሁሉ ፈተና አልፋ ዛሬ ላይ የደረሰች፣አሁን ካለችበትም ግፍና ሰቆቃ ለመውጣት በጀግኖች ልጆቿ በየትግል ዘርፉ ዋጋ እየተከፈለላትና በቅርቡም ነፃነቷን በሕዝቧና በአምላኳ ርዳታ የምትጎናጸፍ በወርቃማ ቃላት ታሪኳ የተጻፈላትና የተዘመረላት ውብ ምድር ነበረች!
ዛሬ ግን ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ትክክለኛ ገጽታዋ ባቅሜ ከላይ እንደ ዘረዘርኩት ነው።ከየትኛውም አቅጣጫ ለሚሰነዘር ገንቢም ሆነ አፍራሽ ምላሽ ብዕሬ ምላሽ ለመስጠት በተጠንቀቅ ላይ ናት።
አምላክ የኢትዮጵያችንን ትንሣዔ ያፋጥንልን!
አሜን
ከህሊና ወንድይራድ
ከመናገሻ
ግንቦት 11/2008ዓ/ም
























































































































No comments:

Post a Comment