Tuesday, March 24, 2015

Interesting comentary on journalism

Yared Hailemariam of Brussels, claims that he is a human rights activist. I found his argument interesting and decided to share it with our readers. I have a large part of the comentary and for those who want to read the full page, I have the link. It starts with the value of journalism, thus:
 
ጋዜጠኝነት ትልቅ ክብር የሚሰጠው፣ የራሱ የሆነ መርህና ስነ-ምግባር ያለው፣ ጠያቂነትን ብቻ ሳይሆን ተጠያቂነትንም በውስጡ የያዘ የሙያ መስክ ነው። ለዛም ነው ጋዜጠኛ የሕዝብ አንደበት፣ አይንና ጆሮ ነው የሚባለው። ሕዝብ በሚከበርበት ቦታ ሁሉ ጋዜጠኛም ይከበራል። ሕዝብ በሚዋረድበት፣ በሚታፈንበትና በሚዋከብበት ስፍራም ጋዜጠኛ ይዋረዳል፣ ይሳደዳል፣ ይታፈናል፣ ይዋከባል፣ ይታሰራል፣ ሲከፋም ይገደላል። ይህም በሕዝብ፣ በመንግሥትና በጋዜጠኛ መካከል ያለውን ቁርኝት በደንብ ያሳያል።

 አንድ ሰው በጋዜጠኝነት ሙያ ሲሰማራ ቢያንስ እነዚህን አምስት መርሆዎች ሊረዳና ሊያከብር ይገባዋል። እነሱም፦

  1. እውነተኝነት እና ትክክለኝነት፣
  2. ገለልተኝነት (ከፖለቲካ፣ ከኃይማኖትና ከሌሎች ሚዛንን ከሚያስቱ አቋሞች)፣
  3. ፍትሐዊነት እና ሚዛናዊነት፣
  4. ሰብአዊነት፣
  5. ለሚሰራዉ ሥራ ተጠያቂነት

."....'ይህን ጽሑፍ እንድጽፍ ወዳስገደደኝ ጉዳይ ልመለስ። ኢትዮጵያ ውስጥ የጋዜጠኝነት ሙያና ሥነ-ምግባር ያለበትን ደረጃና ዝርዝር ታሪኩን በቅጡ የሚቃኝ ጥናታዊ ጽሑፍ የማቅረቡን ሥራ በሙያው ጥርሳቸውን ለነቀሉበትና አቅሙ ላላቸው ባለሙያዎች ልተውና የግል ትዝብቴን ላስቀምጥ። የወያኔ የአገዛዝ ሥርዓት በኢትዮጵያ ላይ ካደረሳቸው ትላልቅ ኪሳራዎች መካከል አንዱ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ማዳፈኑ ነው። ይህን እኩይ ተልኮውንም ለማሳካት በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጠኞችን በተለያዩ ጊዜያት እያሰረ፣ እየደበደበ፣ በሃሰት ክስ እየወነጀለና ከአገር እያሰደደ በማቆጥቆጥ ላይ የነበረውን የሕዝብ ነጻ የመወያያ መድርክ በጨቅላነቱ ቀጭቶታል። ወያኔ ነጻ የውይይት መድረኮችን ለማንጠፍ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። ጋዜጠኞችን በጸጥታ ኃይሎች ማዋከቡና በጡንቻው ማሸማቀቁ አልበቃ ብሎት ሕገ-መንግሥቱን የሚሽሩ ሕጎችንም ጭምር በማጽደቅ አፈናዉን ሕጋዊ አድርጎታል። ይህ አይነቱ በነጻ ሚዲያው ላይ ያነጣጠረው የማያባራ ዱላ ሕዝብ ነጻ የመወያያ መድርክ እንዳይኖረው ከማድርግም አልፎ መደማመጥና መተማመን የማይቻልበት የመጯጯህ ባህልንም ፍጥሯል። እውነትንና እውቀትን መሰረት ያደረጉ የሃሳብ መግለጫ መድረኮች እንዲከስሙ ተደርጎ በምትካቸው ጽንፍ የያዙና በሁለት አፋፍ ላይ ቆመው በጥላቻ፣ በሃሰት፣ ሰብአዊነት በጎደለውና ተጠያቂነት በማይስተዋልበት መንፈስ ውስጥ የተዋጡና ሕዝብን የሚያደናቁሩ የጩኸት መድረኮች ጎልተው እንዲወጡ ተደርጓል።"

"ዛሬ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአገሩ ጉዳይ መረጃ የሚያገኝበት እድል ሁለት ጽንፍ በያዙ እርስ በእርስ ተቃራኒ ነገር ግን ተመሳሳይ ባህሪይ በሚታይባቸው የፕሮፓጋንዳ መድረኮች እጅ ወድቋል። በአንድ ወገን “ልማታዊ ጋዜጠኞች” በግብር ከፋዩ ሕዝብ ገንዘብ በሚንቀሳቀሱትና ሙሉ በሙሉ የወያኔ ልሳን በሆኑት ቴሌቪዥንና ራዲዮ ጣቢያዎች፤ እንዲሁም ነጋ ጠባ ስለ አገዛዝ ሥርዓቱና ስለ ሹማምንቱ በጎ ገድል ብቻ ሲተርኩ የሚውሉ በግለሰቦችና በቡድን የተያዙ ሚዲያዎች (እንደ አይጋ ፎረም፣ ኢትዮጵያ ፈርስትና ሌሎችም)። በሌላኛው ጽንፍ ደግሞ “ሁለገብ ጋዜጠኞች” ለአገሩ በጎ አሳቢ በሆነውና በስደት በሚገኘው ኢትዮጵያዊ መዋጮ እና በፕ/ት ኢሳያስ አፎርቂ ወይም ሻቢያ ድጎማ የሚተዳደረው የግንቦት ሰባት ልሳን ኢሳት ቴሌቪዥንና ራዲዮ ጣቢያ፤ እንዲሁም ለተመሳሳይ ተልዕኮ በቆሙ ጥቂት ድኅረ-ገጾች ናቸው። በእነዚህ ሁለት ጽንፎች መካከል ከላይ የተጠቀሱትን የጋዜጠኝነት መርሆዎች በከፊልም ቢሆን ለማሳካት ካላቸው ቁርጠኝነት የተነሳ እውነተኛና ሚዛናዊ መረጃን ለሕዝብ ለማድረስ የሚተጉትን ሳንዘነጋ ጽንፍ የያዙት መድረኮች በመገናኛ ብዙሃን ስም በአገሪቱ የፖለቲካና ማኅበራዊ ሂደቶች ላይ እያደረሱ ያሉውን ከፍ ያለ ጉዳትና የሚያስከትሉትንም መዘዝ በቅጡ መፈተሽ የግድ ይላል።

ጽንፍ እንኳንስ ጥላቻን ለማራባት ይቅርና ፍቅርንም ለማጠንከር ቢሆን ውጤቱ አድጋ ነው። ጽንፍ ሚዛንን ያስታል፣ እውነትን እንዳናይ ይጋርዳል፣ ፍትሕን ያዛባል፣ ስብዕናን ያራቁታል፣ ለከባድ ስህተትና ውደቀትም ይዳርጋል። ጋዜጠኛም ጽንፍ የያዘ ዕለት ነገር ይበላሻል። እራሱን ብቻ ሳይሆን ድልድል ሆኖ የሚያቀራርበውንም ማህበረሰብ መንገድ ያስታል፣ ያናቁራል፣ ጥላቻ ያሰርጻል፣ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ሆድና ጀርባ በማድረግ ለእልቂት ይጋብዛል። “ልማታዊ ጋዜጠኞች” እና አንዳንድ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ሳይቀሩ የሆድ ነገር ሆኖባቸው ይሁን አምነውበት ከጥዋት እስከ ማት ወያኔ የሰራውንም ያልሰራውንም እያነሱና እየጣሉ፣ ተቃዋሚ ያሉትንም ሲያዋርዱና ሲያበሻቅጡ ስለሚውሉ ሕዝብ እንዲህ ያለውን ፕሮፓጋንዳ መስማት ታክቶታል። የሚረዳው አጣ እንጂ በድሃ አቅሙ ዲሺ እያስተከለ ፊቱን ወደ ውጭ ሚዲያዎች ሲያዞር ማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ግልጽ ነበር። ውሸት መስማት ታከቶናል፣ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ሰልችቶናል፣ አማራጭ አሳቦችንም መስማት እንፈልጋለን የሚል ነው። ወያኔ ሕዝብን ለመስማትም ሆነ ከስህተቱ ለመማር አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ ስለሌለው ከሕዝብ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ ቀጥሏል። ወያኔ ሕዝብን አያዳምጥም፤ ሕዝቡም ወያኔን አያደምጥም።

በሕዝብና በአገዛዙ መካከል የተፈጠረውን ክፍተት ለመጠቀም እድሉና አቅሙ የተፈጠረላቸው የኢሳት አይነት ሚዲያዎችም ሕዝብን ለማስተማርና ለማንቃት፤ እንዲሁም መብቱን ጠንቅቆ እንዲያውቅና ለነጻነቱም እንዲቆም ለማነሳሳት እድሉ ተፈጥሮላቸው ነበር። ይሁንና የኢሳት ተልኮም ሆነ አወቃቀር የግንቦት 7ን ሁለገብ የትግል ስልት መሰረት ያደረገ በመሆኑ በድርጅቱ ጠባብ አጀንዳና የትግል ስልት እንዲወሰን አስገድዶታል። “ሁለገብ” የሆኑ ጋዜጠኞችን አፍርቷል። ችግሩ ሁለገቦቹም ልማታዊ ጋዜጠኞቹ ተንደርድረው የወረደበትን ቁልቁለት ተከትለው አብረው መክነፋቸው ላይ ነው። ሕዝብ አማራጭ ስላጣ ዛሬን ሊሰማቸው ይችላል። አሁን ባሉብት ይዞታ ከቀጠሉ ግን ከሕዝብ ጋር መደማመጥ ይቀርና እንደ ወያኔ ሚዲያዎች በባዶ ሜዳ ማንቋረር ብቻ ይሆናል። ልማታዊ በሆኑት የወያኔ ጋዜጠኞችና ሁለገብ በሆኑት የግንቦት 7 ጋዜጠኞች መካከል ያለው አንድነትም ሆነ ሁለትነት ግልጽ ነው። ሁለቱም ለተለያዩ የፖለቲካ ተቋማት ልሳንነት ማገልገላቸው፣ ጠላት ብለው የፈረጁትን አካል የሚገልጹበት ያልተገራና ጨዋነት የጎደለው ቋንቋቸው፣ ወዳጅ የሆናቸውን ደግሞ ሽቅብ ሚከቡበትና የሚያሞካሹብት ስልታቸው፣ እንዲሁም በብዙ የፕሮግራምና የዜና አቀራረብ ስልታቸውም ጭምር አንድ አይነት እየሆኑ መምጣታቸው ነው። ሌላው ቢቀር አንዱ “አኬልዳማ” ብሎ የድራማ ፊልም ሲሰራ ሌላው “ኦፕሬሽን ሚሊኒየም” በሚል ከአዲስ አበባና ከአስመራ ያሰራጩትነ ዘገባ ልብ ይሉዋል።

ከላይ ከተጠቀሱት የጋዜጠኝነት መርሆዎች አንጻር ሁለቱንም በአንድ ጎራ ተሰልፈው እናያቸዋለን። ልማታዊዎቹ ጋዜጠኞች የወያኔን ባለሥልጣናትና የሻቢያን ተቃዋሚዎች ቅዱስ አድርገው በሚያቀርቡበትና በሚያሞካሹብት መጠነና ልክ ሁሉ ሁለገቦቹም ግንቦት 7ንና አጋሮቹን፤ እንዲሁም የሻቢያ ባለሥልጣናትን በተመሳሳይ ሁኔታ እያቀረቡ በሕዝብ ጉዳይና በፍትህ እንዲያላግጡና እንዲቧልቱ ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ። ለዚህም በቅርቡ የግንቦት 7 ሹማምንትን አጅበው አስምራ የከረሙትን የኢሳት ጋዜጠኞች ቆይታ ልብ ይሉዋል። ልማታዊ ጋዜጠኞቹ የወያኔን ቱባ ባለሥልጣናት ተከትለውና የህውሃት አርማ ያለበትን መለዮ አጥልቀው የድርጅቱን 40ኛ ዓመት ለማክበር መቀሌ እንደ ከረሙት ሁሉ ሁለገቦቹ የኢሳት ጋዜጠኞችም ወታደራዊ ትጥቅና አልባሳትን አጥልቀው አስመራ በሚገኝ ሠራዊት መሃል እየተጎማለሉ የተነሱትን ፎቶና የቀዱትን ቪድዮ ላስረጂነት ማቅረብ ይቻላል።

ሰብአዊነትንም በተመለከተ በሁለቱም ጎራዎች የተሰለፉት “ጋዜጠኞች” ተመሳሳይ የመርህ ግድፈቶችን ሲፈጽሙ ማየት የተለመደ ነው። የዜጎቻቸውን መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች በመግፈፍ. አለም ያወቃቸውን አምባገነኖች እያሞካሹ፣ ወንጀላቸውን እየሸፋፈኑና የሌላቸውን ስብዕና እያለባበሱ ማቅረብ ፍትህን በሚናፍቁት ግፉአን ላይ እንደ ማላገጥ ነው የሚቆጠረው። መለስ ዜናዊንም ሆነ ኢሳያስ አፎርቂን ለሕዝቦቻቸው አሳቢና ባለ በጎ ራዕይ የአገር መሪዎች አድርገው ቢሚያቀርቡ ጋዜጠኞች መካከል ያለው ልዩነት የቆሙለት ወገንና ቦታ እንጂ የመርህ አይደለም። ለብዙ ንጹሃን ዜጎች ህይወት መጥፋት፣ ስቃይና እንግልት ቀጥተኛ ተጠያቂ የሆኑትን እነዚህ አንባገነኖች እየካቡ የፍትሕና የዲሞክራሲ ጠበቃ መሆን አይቻልም። በቅርቡ የኢሳት ጋዜጠኞች ፕ/ር ኢሳያስን ከራሳቸው ሕዝብ አልፈው ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን የሚጨነቁ መሪ አድርገው ለማቅረብ ያደረጉት ሙከራ “የሁለገብ ታጋይነታቸው” ተልዕኮ መገለጫ እንጂ ከጋዜጠኝነት ሥነ-ምግባር የመነጨ አይሆንም። ባለፉት ሃያ አመታት ወያኔና ሻቢያ በሁለቱ አገራት ሕዝብ ላይ ሲፈጽሙት የቆዩትንና ዛሬም እየፈጸሙት ያለውን አስከፊ የሆነ የሰብአዊ መብቶች እረገጣ የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በተደጋጋሚ ያጋለጡባቸውን ሪፖርቶች እነዚህ “ጋዜጠኞች” የሚያዩበት መንገድም ሚዛኑን የሳተ ነው። ልማታዊዎቹ በወያኔ የሚፈጸመውን ጥሰት የሚያጋልጡትን የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በሰደቡበት አንደበታቸው እነዚህኑ ድርጅቶች እያጣቀሱ በኤርትራ ውስጥ ስለሚፈጸመው የመብት እረገጣ ሲተነትኑ በተደጋጋሚ ሰምቻለሁ። ሁለገቦቹ ጋዜጠኞችም የእነዚህን ድርጅቶች ሪፖርት እያጣቀሱ ወያኔ የሚፈጽመውን የመብት እረገጣ ማጋለጠቸው ይበል ቢያሰኝም ሻቢያ በኤርትራ ሕዝብና የሙያ አጋሮቻቸው በሆኑ ጋዜጠኞች ላይ ጭምር የሚፈጽመውን ግፍና በደል እንዳልሰሙ በመምሰልና ችላ በማለት ፕ/ር ኢሳያስን ለሕዝብ አሳቢና መልካም ስብዕና ያላቸው ሰው አድርገው ለማቅረብ መሞከራቸው የሌላኛው ጽንፍ ክሽፈት ነው።

ከላይ እንደገለጽኩት ክፉና አፋኝ የሆነ አንባገነናዊ ሥርዓት በአንድ አገር ውስጥ እረዘም ላለ ጊዜ ሥልጣን ተቆናጦ በሚቆይበት ወቅት ተመናምነው የሚጠፉ በርካታ እሴቶች እንዳሉ ሁሉ በምትካቸውም መጥፎና መረን የለቀቁ አዳዲስ ልማዶች ይፈለፈላሉ። አንዱ ይሄው መደማመጥ የሌለበት የመጯጯህ ባህል ነው። በ1960ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ የጀመረን ይህ ፈሊጥ ዛሬም አለቅ ብሎን ጽንፍ በያዙት በነዚህ መድረኮችም የተለያዩ ሃሳቦች አይንሸራሸሩም። በሃሳቦች ላይ ያተኮረ ውይይትና ክርክር የሚባል ነገርም የለም። ሁሉም የራሱን ብጤ ሰብስቦ ሌላኛውን ወገን ሲወቅጥ፣ ሲራገም፣ ሲያነሳና ሲጥል ነው የሚታየው። ተፎካካሪ ሃሳቦች በማይፋጩበትና በአንድ ጭብጥ ዙሪያ የተለያየ አመለካከት ያላቸው ሰዎች በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውይይት በማያደርጉበት መድረክ ላይ አስር ተናጋራ አቅርቦ ሁሉም ባንድ ሙቀጫ ሌላውን የሚወቅጥ ከሆነ አንዳችም ጠብ የሚል ነገር የለውም። የአንድ ማኅበረሰብ የፖለቲካ አስተሳሰብ ሊሰፋና ሊያድግ የሚችለው በሃሳቦች ዙሪያ በሚደረጉ ምሁራዊ ክርክሮችና ውይይቶች ነው። ጥላቻና ጽንፍ የተረጋጋና የሰለጠነ የፖለቲካ ማህበረሰብ እንዳይፈጠር ትልቅ እንቅፋቶች ናቸው። ሰላማዊ የሆነ የፖለቲካ ሽግግርም እንዳይፈጠር ያደርጋሉ። የፖለቲካ ጽንፍ በያዙ መገናኛ ብዙሃን የሚሰራጩት የጥላቻና የሃሰት ዘገባዎች ቀጥተኛ ተጎጂው አገርና ሕዝብ ነው። የተጀመሩ የሰላማዊ ትግሎች ይኮላሻሉ። ንጹሃን ዜጎችም በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ተታለው ለአደጋ ይጋለጣሉ። ደግ ቀን ሲመጣ እናንተም ለትዝብት ትጋለጣላችሁና ከወዲሁ አስቡበት።

በቸር እንሰንብት!

ያሬድ ኃይለ ማርያም

 

 

 

 

Monday, March 2, 2015

An Ethiopian Episode in PAFF; a Movie for Propaganda or for Erecting National Problem?



A critical Film Review

By Zenebe Tamirat

Title: Triangle- Going to America (Soset Maezen)
Directed by:  Theodros Teshome Kebede,
A Theodros Teshome Kebede Production,
2014 Ethiopia/narrative/ (89 Min) World Premier
On theatre at Baldwin Hills Crenshaw Plaza
The 23 Annual Pan African Film and Arts Festival
February 2015




Ethiopia is little known for its production of films until recent years in which Ethiopian movies began to come up with astounding stories in the form of Video films. The frequency of such video film productions is also exciting leading Ethiopia, to become perhaps, a center of film production in the Horn of Africa. In this process, we also see young and promising Ethiopian actors of high calibor and  hope for the nation. 

Ethiopia, as a nation undoubtedly contains extensive potential and the abundant amount of resources for writers and film producers on which they can base their stories. Concerning Hollywood type full screen films however, very few progress has been made and requires a lot of effort to exploit the numerous resources available in the historic nation.  The recent full-fledged screen film “Teza.” by Haile Gerima was one good example that demanded the application of trained actors and sound investments in cash money. In many of his presentations I have heard Haile, complaining about the lack of finance in his film productions. I think the shortage of finance attribute a lot to the scarcity of Ethiopian full screen film production.

The coming of young film producers, to this line of artistic works, one of whom is Theodros Teshome Kebede who directed the film “Triangle – Going to America (Sost Maezen) [I will cut the long title to “Triangle” here in after,] is also encouraging and may contribute the growth of film production in Ethiopia. The purpose of this paper is to review the film “Triangle” stressing on the story and provide my views to readers.

Watching “Triangle” at the 23rd  “Pan African Film Festival (PAFF) was a pride to all of us who were at the Baldwin Hills Crenshow Plaza, Los Angeles, California. For me it was not only a pride, it was also an exciting experience, as I was wondering what the film was going up to? What was the message? Why was it named “Triangle?” And what were the causes for the absconding of young Ethiopians in the story abandoning their beautiful country? It is therefore proper to thank the film producer and director Theodros for his exertion to bring Ethiopia to this prestigious  movie forum that attracts the eyes of the world every year as the festival takes place. Thus, “Triangle” has become one of the 154 films selected to be seen in the PAFF 2015 thanks to Theodros and the excellent young actors and actresses who deserve our appreciation.

The film is all about the story of a group of young Ethiopians who opted to take a dangerous route to seek asylum in the United States rather than enjoying life in beautiful Ethiopia. But why abandon the beautiful Ethiopia? Tringle says, it was “stupidity,” unnecessary venture taken by the immigrants while life was comfortable at home. It sends a message that some flee their country for a reason of poverty, (the two brothrs in the film who regret falling into such a horrible risk to bring out their mother from poverty.) Some for escaping the preasure that is being made on marriage issues (the young girl who opted to abondon her country for the sake of marrying Jemal, a muslim youth lover) , and some for dissatisfying in living in Ethiopia in general (The young man in the film who lost his wife during the journey).

The route does not not show its start point but indicates that it was an arduous journey that involves, long distance walking in a hostile desert, comfrontation with dishonest guides, dangourous sea voyage and  extended journey in uncomfortable dumping trucks.

One other thing I was wondring about was the word “Triangle”  in the title. You find this at the end of the film to be related to the three sides of coninents that the immigrnts route took place. The immigrants start from the continent of Africa and head North-East (Presumably through the Sudan up ward to North East Africa crossing the desert by foot and by by dump trucks),  then crossing the Meditranean by boat and finally flying to Mexico by plane to continue the journey by a wagon and half way by foot to the U.S.A.

This was again elaborated on the question and answer session by the film director, Theodros, who said that the title was taken from the history of Slavery,  to depict the fact that Ethiopians who abondoned their country for a better life abroad have voluntarily chosen modern slavery.

The term “Triangle” is related to the Trans-Atlantic Slave Trade of the 16th Century that streaches its base line from Britain in Europe to the Caribean Island and connecting the the tips of the adjusccent lines on the West Coast of Africa. (See the Abolation Project:  abolation.e2bn.org/slavery_43.html).

Tewodros is trying to compare the modern immigration to the U.S. to the compulsory slavery of Africans in the 16th Century. But what he lost in this comparison is that the core cause of abandoning the beautiful Ethiopia, which is absolutely “political.” In my view I see the comparison between the two immigrants differently. Contrary to Tewodros's opinion, I see  the former as being compulsory and for enslaving the immigrants and the later as voluntary to escape clampdown with a motto of attaining independence in latter days. In fact I do not consider the former as “immigration” but as “displacement.”  Again contrary to Tewodros’s thinking who sees the cause of the problem in the later case as “stupidity,” I see the problem as the failure of the Ethiopian dictatorial Government to entertain its citizens with the necessary freedom to work and develop their country. I see the Government as an entity that  failed to establish the necessary democratic system and good governance that is required to develop private ownership. I consider the forcible application of ethnic based ruling system in which a selected ethnic group, the “Tigre”   ethnic group” is considered as a supreme power responsible for illegal immigration.

Due to the ethnically centered policy of the TPLF, Ethiopians of all other groups are harassed, intimidated, imprisoned and killed in the streets without the due process of law. Citizens of young ages including school boys are shot while going to school or returning from school. There is no political freedom and when demanded the answer is “bullet in the head.” This is the main reason for abandoning beautiful Ethiopia leaving it behind for the Tigreans to enjoy it. The film intentionally abandons to reveal the main causes for illegal immigration from Ethiopia. Instead it beats around the bush to replace the actual facts by other irrelevant reasons.

Commenting on my view that the film fails to present the fact on the ground for the cause of mass immigration from Ethiopia, Theodros says first he is not a politician to comment on my view and second he says Ethiopians must fight for their rights at home as the Americans are doing.  Here, he forgets the fact that Americans have established a democratic system following the 1776 revolution and need not abandon the well set American democracy.

I argue that, despite the producer’s claim that the film is non-political, the reflection of the movie sides with the current rulers.  It advocates life in Ethiopia was beautiful and manageable as if there exists freedom of speech, writing, freedom to own land and other properties and freedom to the pursuit of happiness. By inserting the term “Triangle,” it tries to tell us that slavery still exists in the United States whereas the fact on the ground shows  my fellow Ethiopians are slaves under their own Government forbidden even the least need of human rights such as owning their own shelters.

I also argue coming to America, particularly to the United States has nothing to do with slavery and cannot and should not be compared to the 16th century slave trade as the title of the film indicates. The Ethiopian Diaspora in the United States is equally treated with those born in America in all spheres of employment, ownership of property and the pursuit of happiness, voting and other democratic processes. Today, Ethiopians in the U.S. comprise of engineers, doctors, and other profound professionals contributing to the struggle at home as well as to the economic and social growth of the U.S.

The United States is a land of immigrants who abandoned their origin due to various suppression and oppression. The constitution thus compromise the respect of all human rights and the contents there in are inviolable. The United States today has proved itself a nation that provides all opportunities including the possibility of becoming president of the United States  to all disregarding who came first or last, black or white. America is no more a land of  slave drivers. So, that title, of the film, “Triangle” is incorrect and improper.

Ethiopians at home suffer from employment just because they are non-Tigreans. Despite the fact that the Tigreans in Ethiopia are minority, statistics show that they are more employed than the majority Oromo and Amhara ethnic members. This is not a surprise because the Tigrean party controls the economy with its numerous Trade, and Industrial companies that feed it with billions of dollars. These companies offer  employment opportunity primarily to Tigreans. The film fails to reveal this fact . It also fails to show what alternative then has the rest of the youth to sustain its life when the gun is pointed at its forehead and the door to employment is slummed behind it?

It is true that the youth has to fight for its rights inside Ethiopia but the struggle should also continue outside of Ethiopia too for the purpose of strategy to win the fight.  The fight at home needs the support from the Diaspora in the form of knowledge, experience, finance and foreign relations. Therefore Tewodros's thought of stay and die in Ethiopia as the three hundred Spartans died in Sparta is a time passed and harmful thought.

The struggle is not as simple as Tewodros thinks it to be. The dictators at home are supported by world powers such as the United States allocating hundreds of millions of dollars in support of annual budget a good part of which goes to suppress democracy. China is another big power supporting suppression in return to its interest of dumping Chinese workers in Ethiopia. Britain, France and Saudi Arabia are all supporters of the dictators at home. For example, recently the ruling Tigrean Party TPLF disbanded leaders of  a major party “Andenet” that comprises, a vast majority of the Oromo and Amhara Ethnic group members and replaced it with its satellite individuals.  This party was an example of a youth group fighting to establish a democratic Ethiopia  within the inside. But the attack on the party was harsh. The need to change such kind of dictatorship requires to integrate the struggle harmoniously from inside and outside of Ethiopia.

The Diaspora is not engaged in biting hamburgers only as Tewodros thinks but much more than that. The Diaspora, other than wining the demanding life in exile it actively works to bring about changes in the lives of Ethiopians at home. The three billion dollar transfer per annum from the pocket of the Diaspora is a living witness for what I am saying here. By the way, Tewodros,  hamburger is not a luxury food in the U.S but the least alternative for the poor to eat.     

In the Question and Answer briefings a brilliant question that says “How many of the people want to abandon Ethiopia as the film depicts” was raised by one of the spectators. The reply by Tewodros was awful. He says 40% of the population of Ethiopia, 36 million, people want to abandon Ethiopia. This is extremely exaggerated and misinforming the American public with wrong data. My view on this issue I stated at the spot was that there are no so many people in Ethiopia  that match the said figure who know the existence of the United States. A large number of people in Ethiopia live in the country side without formal education. The number of people that went to elementary school does not exceed 15%. I do not know the exact figure of how many people may wish to come to the the United States, but I can guess that does not exceed 1% of the 15%. Calculating the maths, we can say round about 135,000 may wish to come to the United States. This is not a big number compared to those who want to come to the U.S. from other countries of the world including Europe.

The Amharic literature in the film is satisfactorily right. It seems well written and in some parts the expressions touch the hearts of their audiences. The film illustrates the characters of Ethiopian folks vividly. Honesty, loyalty and bravery are some of the characteristics well reflected in the movie. I do not know how much it is true, but loyalty is less reflected in the case of the Eritreans character. By a part in which Eritreans abandon a malaria attacked female friend of them, the producer tries to illustrates the betrayal characteristics of Eritreans. On the contrary by a part in which the Ethiopians help this same girl, the film boosts the kindness of Ethiopians even to the turncoat Eritreans. This may be taken as a response to the separation of Eritrea from Ethiopia.The producer seems also to try to show that there is no hard feeling between ordinary Ethiopians and Eritreans because of the political separation.

What is strange in the making of this film is the round about route to the United States. The regular illegal immigration route known is crossing the Sudan border and stay in refugee camps thereby wait until the UN  arranges refugee status   acceptance in the U.S. or Europe. The way to Europe, Italy and having visa from Italy and a flight to Mexico as illustrated in the film is  strange and unattempted.  What surprises me most in the movie was the illegal crossing of the U.S border in collaboration with Mexican mafia group. One wonders what was the use of the Italian visa issued to the immigrants.

Lastly, the confrontation with the Mafia was interesting. It depicts the real Ethiopian character of bravery. “Leave you alone, even the Italians could not frighten me” murmurs one of the Ethiopians who finally gripped the neck of the chief of the mafia  with one hand pointing a gun on his victim’s head with the contrary. This is a real part that drives spectators with emotion. In fact I was beyond control of my emotion for a while.

The final blast however begs the question, “What was the LAPD doing when a war was going on in its territory.  All in all, in my view, the result of the film is  mixed with good and bad. The actors and actresses are astounding and as excellent as they always were in their video movies. The literature in the movie is good enough. The production is competitive. Unfortunately the movie fails to depict the fact why Ethiopians take such a risky venture seeking for asylum abroad in spite of the fact they own a beautiful and resourceful country. Missing this important point of critically revealing the objective reality in Ethiopia,  reduces the movie to a status of an instrument of Propaganda rather than a tool for rectifying the social, economic and political problem of the country.




The writer, Zenebe Tamirat is available at ztamira@yahoo.com