Friday, October 7, 2011

Prof. Mamo Muche Inducted to ASSAF; Calls for Submission of Research Papers

The celebrated scholar Mamo Muche was inducted to Academy of Science of South Africa (ASSAF), the website, http:// www. Ethiopia.Org reported. The noted scholar is a distinguished Professor at the Institute for Economic Research (IERI) at the Tshwane University of Technology, Pretoria, South Africa and has produced a number of research papers on various fields of discipline. For more on the news please go to http://www.ethiopia.org/pdf/Mammo_Muchie.pdf
In related news, Dr. Muche calls on scholars to submit research papers in the 2nd Africa Liberation International Symposium. Deadline for abstract submission is October 31. Those who are interested may contact Professor Muche via telephone numbers +27123823078, Fax +2712383071 or just shoot him an e-mail at muchiem@tut.ac.za/mammo@ihis.aau.dk

Thursday, October 6, 2011

የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ስለመፈታት

Selam Ato Zenebe,

I have pasted my letter to VOA on your " comment" space. You are most welcome to use it should you wish to. But your inclusion of the EPRP and AESM  prisoners will be v. welcome.

With my best,



በአሜሪካን ሬዲዮ ለአማርኛው ክፍል አዘጋጆችና አቅራቢዎች፦

የሰላምና የጤና ምኞቴ ለኹላችሁም ትድረስልኝ ።

ስለዚህ ጉዳይ የጎረፉትን ብዙ የድጋፍና የተቃውሞ አስተያይቶችን በእናንተው አማካይነት ከሰሙት ውስጥ አንዱ ነኝ። እኔ ግን አስተያዬቴንና ስሜቴን ለራሴ ይዤው ቆየሁ።ይህን የሚሰማ፦ እናንተ ለሕዝብ ጆሮ ካበቃችሁት፦ "ለምን?" ሊለኝ ይችላል። ቢልም መብቱ ነው። መልሱን እናንተው ትሰጡልኛላችሁ ብዬ አምናለሁ፤፡ እናንተ ግን ልትመልሱልኝ የማትችሉት እነርሱ እስር ላይ ኾነው መልስ ሊሰጡኝ በማይችሉብት ኹናቴ  ብዬ መቆጠቤን መምረጤን ነው።

በቀደምት፦ የየዕምነቱ መሪዎች ለዚህ መነሳታቸው የየዕምነታቸው ኃላፊነታቸው ጎትጐቷቸው ነው? ወይስ በገዢዎችቹ "ቹ!" ባይነት? የዕምነት ግዳጅነት ከኾነ ለምን በየወኅኒው፡ የኦነግ፦ የኦብነግ ወዘተ ደጋፊዎች ናችሁ ተብለው ለአሠርተ ዓመታት ያለፍርድ መታጎራቸውን ያለ ጥፋት የታሠሩት የቅንጅት መሪዎች ሲፈቱ በነገሩን መሠረት ሄደው አጣርተው ወይ እንዲፈረድባቸው አልያም እንዲፈቱ አላደረጉም? አንዳንድ ጊዜስ ሃይማኖታቸው ከሚያዝዘው ውጪ የወንጀሉ ተባባሪያን አልኾኑም? እንዲያዉም ፍርድ ቤት ሲለቅቃቸው እነዚሁ የ "ሃይማኖት አባት ነን " ባዮች( አኹንም የሃይማኖቱን ይግባኝ የሌለውን ትእዛዝ አፍርሰው) ወደ ወኅኒ አልመለሱም?
ከነዚሁ ውስጥ በየወኅኒው ሰበከታቸውን በነጻ እያኪያሄዱ ስንቱን ወደነርሱ ሲለውጡ ያለፍርድ ስለታጎሩት ምነው ማንሳት አልፈለጉ?
ታዲያ ሕዝቡ ሽምግልናቸውን የእምነት ሳይኾን የማስመሰልና የምድራዊ ታዛዥነት ነው ቢል ይፈረድበታል?
እምዬ !! አይዞሽ!! በምድራውያኑም መንፈሳዊም ነን በሚሉትም ትበደዪ? በቅርቡ በይገላግልሻል!

ወንጀለኞቹ "ሕዝብንና መንግሥትን ይቅርታ ጠይቀው" ተብሏል - ይባላል" አንደኛ ሕዝብ ሲባል ምን ማለት ነው? ለእኔ ይህ ክፍል ለሦስት መከፈሉ ይታየኛል፦
 - ለፍርድ ትቀርባላችሁ ተብለው " ፍርድማ ከኾነ ምንገድዶን፦" በማለት በሥራቸውና በሕግ ተማምነው  ወደ ፬ኛ ክፍለ-ጦር
   ተሽቀዳድመው እየገቡ፦   በአርበርኝነት አካላቸው በጥይትወንፊት ኾኖ በታምር የኖሩት ሳይቀሩ በዓለም ሸንጎዎች ላይ  
   ለአገራቸው በክብር  የተሟገቱናየረቱልን ሳይለዩ፦ ለአብነት ያህል፦ እንዲያው በአጠቃላይ የታሪክ ባለሞያዎችና የታሪክ
   ምስክሮች የነበሩት የተርሸኑ ቤተሰቦች

 - በየሰበባ ሰበቡ ( ሽብሮች) አሰቃቂ ግፎች ተፈጽመውባቸው በገዛ አገራቸው አልቅሰው እንዳይቀብሩ የተከለከሉት ቤተሰቦች
   ባህልናሥርዐትን አጥፍተው ተከታታይ ትውልዶችን እንዲዋዥቁ የተደረጉባቸው አዛውንትን

- አገርን በጎሳ በሃይማኖት ወዘተ ከፍለው ይባስ ብለውም ባሕር አልባ ያደረጉትን ሕዝብ እንዴት ብለውና አድርገው ነው 
  ይቅርታ የጠየቁት? የትና መቼ ነው ይቅርታ የጠየቁት?

ይባስ ብለው ደግሞ "መንግሥትን ይቅርታ ጠይቀው ተብሏል። ይሄ ፈጽሞ ሊዋጥልኝ ያልቻለ ጉድ ነው። በሽፍትነት ጊዜያቸው ዓላማቸውን ዐውቆ ሲዋጋቸው የነበሩትን ነው ይቅርታ የሚጠይቁት?

ለደርግ እኮ አንድ አዎንታዊ ነገር ቢኖረው "ለኢትዮጵያ አንድነት ተዋግቷል" ነበር። ሹሞቹ መንግሥት ተብዬውን ይቅርታ ከጠየቁ የክብር ርዝራዤያቸውን ራሳቸው አመከኑት ማለት ነው። በገዛ ጥፋታቸው አገርን እንዲህ ዓይነት አዘቅት ውስጥ መጣላቸው አንሶ!

አምላክ ይቅር ይበለን፦

ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ